Warning: mkdir(): No space left on device in /var/www/tg-me/post.php on line 37

Warning: file_put_contents(aCache/aDaily/post/kaletsidkzm/--): Failed to open stream: No such file or directory in /var/www/tg-me/post.php on line 50
ቃለ ጽድቅ ዘመካነ ሕይወት | የመ/ሕ/ሰ/ት/ቤት ሰሌዳ መጽሔት ንዑስ ክፍል | Telegram Webview: kaletsidkzm/9086 -
Telegram Group & Telegram Channel
#ቅዱስ_ኤፍሬም_ስለ_ልደተ_ክርስቶስ_እንዲህ_አለ፦

ጌታ ሆይ ቅድስት እናትህ ድንግል ሳለች አንተን ፀንሳ በመውለድ እናትነትን ገንዘቧ አደረገች፤ ድንግል ሆና ሳለች ከጡቶቿ ወተት ፈሰሰ፤ ድንግል ከሆነች መሬት ንጹሕ ምንጭ እንዲፈልቅ፤ እንዲሁ ድንግል ከሆነችው እናትህ ጡቶች ወተት ፈለቀ፡፡ እርሱዋ አንተን ብትሸከምህ አንተ ጽንዕ ሰጥተሃት ነው፤ በተራብክ ጊዜ አንተን ከጡቶቹዋ ትመግብህ ዘንድ፣ ነቢዩ ዳንኤል በታላቅ ተራራ የመሰለህ አንተን አንደ ሕፃናት ታቀፈችህ፤ በፈቃድህ የተጠማህ አንተን በእጆቹዋ በፍቅር ትዳብስህ ዘንድ፤ የምህረት እሳት የሆንኽ አንተ ክንዶቿን መለኮታዊው እሳት እንዳይቃጥላቸው ጠበቅኻቸው፡፡

ጌታ ሆይ እናትህ ግሩም የሆኑ ተአምራት የተፈጸሙባት መካን ናት። ወደ እርሱዋ የሁሉ ጌታ የሆነው ገባ፤ የአገልጋዩን አርአያ ነስቶ ተወለደ። የእግዚአብሔር ቃሉ የሆነ እርሱ ወደ እርሱዋ ገባ፤ ዝምተኛ ሆኖ ተወለደ። ነጎድጓድ የሆነው እርሱ ወደ እርሱዋ ገባ፤ ጭምት ሆኖ ተወለደ። እረኛ የሆነው እርሱ ወደ እርሱዋ ገባ፤ በግ ሆኖ በመወለድ በአባግዕ ቋንቋ ተናገረ፡፡

ጌታ ሆይ የእናትህ ማኅፀን ከተፈጥሯዊው ሥርዓት በተቃራኒው ፈጸመ፤ ሁሉን ያከናወነ በባለጸግነቱ ወደ እርሷ ገባ፤ ደሃ ሆኖ ተወለደ። ከሁሉ በክብር የሚልቀው እርሱ ወደ እርሷ ገባ፤ ትሑት ሆኖ ተወለደ። በክብሩ ገናና የሆነው እርሱ ወደ እርሱዋ ገባ፤ የባሪያውን መልክ ይዞ ተወለደ። ብርቱ የሆነው እርሱ ወደ እርሱዋ ገባ፤ ጥበቃ እንደሚያስፈልገው ሕፃን ሆኖ በማኅፀን ተገኘ። ፍጥረትን ሁሉ የሚመግበው መራብንና መጠማትን ገንዘቡ አደረገ፤ (አጣጣመ) ሁሉን በበረከቱ የሚያለብሰውና የሚያስጌጠው እርሱ ራቁቱን ተወለደ።

እኛን ለማዳን ሲል የእኛን ተፈጥሮ ገንዘቡ ላደረገ ለእርሱ ክብር ምስጋና ይሁን።

መልካም በዓለ ልደት......

tg-me.com/kaletsidkzm/9086
Create:
Last Update:

BY ቃለ ጽድቅ ዘመካነ ሕይወት | የመ/ሕ/ሰ/ት/ቤት ሰሌዳ መጽሔት ንዑስ ክፍል

Share with your friend now:
tg-me.com/kaletsidkzm/9086

View MORE
Open in Telegram

ቃለ ጽድቅ ዘመካነ ሕይወት | የመ ሕ ሰ ት ቤት ሰሌዳ መጽሔት ንዑስ ክፍል Telegram | DID YOU KNOW?

Date: |

Why Telegram?

Telegram has no known backdoors and, even though it is come in for criticism for using proprietary encryption methods instead of open-source ones, those have yet to be compromised. While no messaging app can guarantee a 100% impermeable defense against determined attackers, Telegram is vulnerabilities are few and either theoretical or based on spoof files fooling users into actively enabling an attack.

What is Telegram?

Telegram is a cloud-based instant messaging service that has been making rounds as a popular option for those who wish to keep their messages secure. Telegram boasts a collection of different features, but it’s best known for its ability to secure messages and media by encrypting them during transit; this prevents third-parties from snooping on messages easily. Let’s take a look at what Telegram can do and why you might want to use it.

ቃለ ጽድቅ ዘመካነ ሕይወት | የመ ሕ ሰ ት ቤት ሰሌዳ መጽሔት ንዑስ ክፍል from sg

Telegram ቃለ ጽድቅ ዘመካነ ሕይወት | የመ/ሕ/ሰ/ት/ቤት ሰሌዳ መጽሔት ንዑስ ክፍል
FROM USA